loading
በኢንዶኔዥያ ርእደ መሬት ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ፡፡

ሎምቦክ በተባለችው ደሴት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ400 ሰዎች በላይ ህይዎታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡
ቻናል ኒውስ ኤዥያ እንደዘገበው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ድረስ ከፈራረሱ ህንጻዎች ስር የተቀበሩ ሰዎችን የማፈላለጉን ስራ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
የኢንዶኔዢያ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ሱቶፖ ፑሮ ኑግሮሆ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መረጃ 436 ሰዎች ሲሞቱ 1 ሽህ 300 የሚሆኑት ቆስለዋል፡፡ ቁጥራቸው 350 ሽህ የሚጠጋ ነዋሪዎች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ካካባየቸው ርቀው ተሰደዋል፡
እስካሁን በደረሰው አደጋ የወደመውን ንብርት ጨምሮ ሰዎችን ለማጓጓዝ ከ5 ትሪሊዮን የሀገሪቱ ገንዘብ ሩጲያ ወይም ሶስት መቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ መድረሱንም ባለስልጣናቱ ተናግረዋል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *