loading
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛሉ፡፡

የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባለድሉ ጅማ አባጅፋር እ እንደ ኦኪኪ አፎላቢ እና መሰሎቹ ወደ ሌላ ክለብ ማምራታቸውን ተከትሎም የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት እስካሁን በአጠቃላይ 11 ያህል ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡
በትላንትናው ዕለትም ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተሰናበቱት አሉላ ግርማ እና ዘሪሁን ታደለ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቡናው አስቻለው ግርማ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሁነዋል።
ወደ ዋናው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን በማደግ እና በፍጥነት የመጀመርያ ተሰላፊ የመሆን እድል ያገኘው አሉላ ከክለቡ በተጨማሪ የብሔራዊ ቡድን ተመራጭ ሲሆን ከክለቡ ጋርም ውጤታማ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል። ነገር ግን ያለፉትን ሁለት ዓመታት በጉዳት ምክንያት ተስፋ የተጣለበትን ያህል እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻለም ይህን ተከትሎ ከፈረሰኞቹ ጋር ተለያይቶ በሁለት ዓመት ውል ለጅማ ፈርሟል።
ሌላኛው የቡድን አጋሩ ግብጠባቂው ዘሪሁን ታደለ እንደ አሉላ ሁሉ በሀለት ዓመት ውል ጅማን ረግጧል ። ዘሪሁን ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ግብ ጠባቂ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት በሮበርት ኦዶንካራ ምርጥ ግብ ጠባቂነት የመሰለፍ እድል ሳይሰጠው ቆይቷል፡፡ እድል አገኘም ከተባለ ኦዶንካራ ጉዳት አሊያም በማይኖርበት ጊዜ ነበር፡፡
አስቻለው ግርማም ወደ ጅማ አምርቷል። አስቻለው በቡና ቆይታው ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል። ተጫዋቹ በጅማ የአንድ ዓመት ውል ፊርማን እዳሰቀመጠ ተነግሯል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር እስካሁን በአጠቃላይ በዝውውር መስኮቱ 11 ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል።

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከከፍተኛ ሊጉ መሸጋገር የቻለው ባህርዳር ከነማ ተጫዋቾችን በማስፈረም ለ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተዘጋጀ ይገኛል፡፡
በአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው (ማንጎ) የሚመራው የጣናው ሞገድ አማካዩን
ታዲዮስ ወልዴ ከወላይታ ዲቻ የመጀመርያው ፈራሚ አድርጓል።
በተጨማሪም አማካዩን ኤልያስ አህመድ ከሠበታ ከነማ ክለቡ በፕሪምየር ሊጉ ክፍተቱን ሞልቶ የተሻለ ተፎካካሪ ለመሆን አስፈርሟል፡፡
ክለቡ አብረሃም ታምራትን ከኢትዮጵያ መድህን በ1 ዓመት ኮንትራት ውል አስፈርሟል፡፡ የጣናው ሞገድ 3ኛው ፈራሚ መሆን ችሏል፤ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ነው፡፡
የመስመር አጥቂው እንዳለ ደባልቄን ደግሞ ከ ጅማ አባ ጅፋር ወደ ክለቡ ቀላቅሏል፡፡
ባህርዳር ከነማ የነባር ተጨዋቾችን ውል ከማራዘም ይልቅ አዳዲስ ተጨዋቾችን በማዛወር ተጠምዷል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *