ወደባንኮች መጥተዉ የዉጭ ምንዛሪን ወደ ብር የሚቀይሩ ሰዎች ቁጥራቸዉ እየጨመረ ነዉ ፡፡
ወደባንኮች መጥተዉ የዉጭ ምንዛሪን ወደ ብር የሚቀይሩ ሰዎች ቁጥራቸዉ እየጨመረ ነዉ ፡፡
አስተያየታቸዉን ለአርትስ ቲቪ የተናገሩት የባንክ ሰራተኞች እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የዉጭ ምንዛሪ መመንዘር ያለበት በባንክ ብቻ ነዉ፤የዉጭ ምንዛሪ በእጃችሁ የያዛችሁ ባስቸኳይ ወደባንኮች አስገቡ ካልሆነ የተለየ ዘመቻ ይኖራል፡፡“ ካሉ በኋላ የዉጭ ምንዛሪ ተጠቃሚዎች ወደባንኮች እየመጡ ነዉ ብለዋል፡፡
አንዳንዶች ለዉጡን በመደገፍና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ በመቀበል ወደ ባንክ የመጡ ሲሆን ፤አንዳንዶቹ ደግሞ ቀጣይ በዶክተር አብይ ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎችን በመፍራት የመነዘሩ እንዳሉ የባንክ ባለሞያዎቹ ተናግረዋል፡፡
የባንክ ተጠቃሚዎችም በጥቁር ገበያ የዉጭ ምንዛሪ ዘርዛሪነት የሚታወቁ እንደ ኢትጵያ ሆቴል ጀርባ አከባቢዎችም አላፊ አግዳሚዉን “ምንዛሪ ነዉ? “ ከሚል ጥያቄ ገላግለዉታል ብለዋል፡፡
መንግስት የዉጭ ገንዘቦች በባንኮች ብቻ እንዲመነዘሩ እና ሌላ ቦታ ያሉ ገንዘቦች ባንክ ዉስጥ ብቻ እንዲቀመጡ ለማበረታታት በፊት በባንኮች ይጠየቁ የነበሩ ዝርዝር ጥያቄዎች ለግዜዉ እንዲቀር ማድረጉም የዉጭ ምንዛሪ ወደ ባንኮች እንዲመጣ ማገዙን የባንክ ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡