የኤርትራ እና የኢትዮጲያ በጋራ የመስራት ቁርጠኝነት አሰብን እስከመካፈል ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
የኤርትራ እና የኢትዮጲያ በጋራ የመስራት ቁርጠኝነት አሰብን እስከመካፈል ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
ትላንት የመደመርን ጽንሰ ሀሳብ በማባዛት ፣ማካፈልና መቀነስ ጭምር ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማካፈል ዉስጥ አሰብንም በጋራ መካፈል የምትለዉ ንግግራቸው ባትብራራም ብዙዎችን አስፈንድቅዋል፡፡
ማረጋገጥ እወዳለሁ በሚል ማረጋገጫ ቃል የተደመደመዉ የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአማረኛ ንግግርም፤ የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት መቼም ወደኋላ እንደማይመለስ አረጋግጠዋል፡፡
ትላንትና በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው የሰላም ማብሰሪያ መድረክ ላይ የተረሱ አንድነትን የሚሰብኩ ሙዚቃዎችም ተጋብዘዋል፡፡ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና ሌሎቸም ታዋቂ ግለሰቦች ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ አንጋፋዎቹ አርቲስቶች እነ መሃሙድ አህመድ፣ አሊ ቢራ፣ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ስለሺ ደምሴ፣ ነዋይ ደበበ፣ፀጋዬ እሸቱ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከወጣት ድምጻዊያን አጫሉ ሁንዴሳ ና ቴዎድሮስ ካሳሁን ተገኝተዋል፡፡