የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ሹም ሽር ሊያካሄድ ነው ተባለ፡፡
ሪፖርተር እንደዘገበዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የካቢኔ አባላት ሹም ሽር ሊያካሂዱመሆኑ እና ከመጠን በላይ በመስፋታቸው ምክንያት ለአሠራር አላመቹም የተባሉ መሥሪያ ቤቶች እንደሚታጠፉ ተነገሯል፡፡
ከፌዴራል መንግሥትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ አመራሮች፣ እስከ ቀጣዩ ምርጫ ድረስ የካቢኔ አባል ሆነው የሚሠሩ ተሿሚዎች እየመለመሉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 34 የካቢኔ አባላት ያሉት ሲሆን፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአዲስ አመራር ይተካሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር እንደዘገበዉ