ሜይ የአውሮፓ ህብረትን እንድከስ ትራምፕ መክረውኛል አሉ
ሜይ የአውሮፓ ህብረትን እንድከስ ትራምፕ መክረውኛል አሉ
የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ ከቢቢሲው ጋዜጠኛ አንድሪው ማር ጋር ባደረጉት ቆይታ ትራምፕ ከነሱ ጋር ለድርድር ጊዜ አታጥፊ ይልቁንም ክሰሻቸው ብለውኛል ብለዋል፡፡
ትራምፕ እንግሊዝን በጎበኙበት ወቅት ነው ይህን ምክር ለጠቅላይ ሚንስትሯ የለገሷቸው፡፡
ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሌላ ንግግራቸው ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ የብሪኤግዚት ጉዳይ ከአቅማቸው በላይ የሆነ ይመስላል፤ ለዚህ ስራ በቅርቡ ስልጣናቸውን የለቀቁት የውጭ ጉዳይ ሚንስተሩ ቦሪስ ጆንሰን የተሻሉ ነበሩ ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡