loading
አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ቤት ሆኖ መስራትን እንደ አማራጭ እያጤነችው መሆኑ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ቤት ሆኖ መስራትን እንደ አማራጭ እያጤነችው መሆኑ ተነገረ፡፡
በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ተከትሎ የአውስትራሊያ ዜጎች ቤታቸው ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ እና ጭምብል እንዲለብሱ ተጠይቀዋል።


ሀገሪቱ በአዳዲስ የኦሚክሮን ተህዋሲ የሶስተኛ ዙር ማዕበል ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተጠቂዎችን መጨመር ለመቋቋም የሁለተኛ ምዕራፍ ክትባቶችን ተደራሽ አድርጋለች። በሀገሪቱ ዕለታዊ የኮቪድ ተያዦች ቁጥር ከ50 ሺህ በላይ ከፍ ያለ ሲሆን ይህም በሁለት ወራት ውስጥ
ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።


የሀገሪቱ የጤና መኮንኖችም በቅርቡ ወደ ሆስፒታል የሚገቡት ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከፍተኛ እንደሚሆን የተነበዩ ሲሆን ቢያንስ ለአጭር ጊዜ አንዳንድ ሁኔታዎችን በተለየ መንገድ ማድረግ አለብን ብለዋል። በዚህም የቫይረሱን የስርጭት መጠን ለመግታት ስራዎችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ መከወን ግድ ይላል
ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከቤት ሆነው መሥራትን በኩባንያዎች እና በሠራተኞቻቸው መካከል ያለ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ለአንዳንድ ሰዎች በቀላሉ የማይቻል መሆኑን ተናግረዋል። ሰራተኞች ደህንነታቸውን መጠንቀቅ አለባቸው የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመተባበር መንፈስ ከተጉ የተጋረጠባቸውን ችግር እንሚሻገሩ ተናግረዋል ሲል አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *