በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ::
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ:: ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሰጠ፡፡ ሆስፒታሉ በሴት ሐኪሞች ብቻ በሚመራው በዚህ መርሀ ግብሩ ለ23 ያህል ሕሙማን ቀዶ ሕክምና እሰጣለሁ ብሏል፡፡
የሴቶች ሕክምና ቡድኑን የሚመሩት ዶ/ር መሰረት ሕይወቴ የቀዶ ሕክምና ቡድኑ ከቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶች አንስቶ የተለያዩ ሴት የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ መሆኑን ገልፀዋል። አገልግሎቱ ቀዶ ሕክምና የተሰራለት ታማሚ ወደ ሙሉ ጤንነቱ እስኪመለስ ድረስ የሚደረግለትን ክትትል ጭምር ያጠቃለለ መሆኑንም ተናግረዋል።
የቀዶ ሕክምና ቡድኑ ዓላማ የዓለም የሴቶች ቀንን ከመዘከር ባሻገር ለሴቶች ከባድ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ስራዎች በሴቶችም እየተሰሩ እንደሆነ ለማሳየት ነው ብለዋል። በተጨማሪም የፆታ መድልዎ እንዲወገድ ለማድረግና እና “ይቻላል!”ን ለማስተማር መሆኑን ዶ/ር መሰረት ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።