loading
ተቋርጦ የነበረዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር መድረክ ዛሬ ተካሄደ

ተቋርጦ የነበረዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር መድረክ ዛሬ ተካሄደ

16 ፖለቲካ ፓርቲዎችን የያዘዉ መድረኩ የድርድሩ መዘግየትን በተመለከተ ቀዳሚ መወያያ ርዕሰ ጉዳዩ ያደረገ ሲሆን ምክንያቱም በደቡብ ክልልና በቤንሻንጉል ክልል ተከስቶ የነበረዉ የጸጥታ ችግር እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ጉዳዩ ይመለከተዋል የተባለዉ የኢህአዴግ ፓርቲ ሲሆን ፤የርፓቲዉ ተወካይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ዉይይቱ ብሔራዊ መግባባትን በተመለከተ ተደራዳሪዎቹ ፓርቲዎች ያስቀመጡትን አጀንዳ በማየትና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የብሔራዊ መግባባት ድርድሩ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በዛሬዉ የፓርቲዎቹ መድረክ የኢትዮጵያ አንድነት ኮንግረስ ፓርቲ ወደ ተደራዳሪዎቹ ለመቀላቀል ያቀረበዉ ጥያቄም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡የኮንግረሱ መሪ አቶ ገረሱ ገሳ እንደተናገሩት ከዚህ በፊትም ድረድር ዉስጥ ነበርን ፤አሁን ደግሞ እንደ አዲስ ተጠናክረን ወደ ድርድሩ ተቀላቅለናል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *