የኢትዮጵያን ስም የሚያጠለሸው አዋጅ ውድቅ ተደረገ::
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 ኢትዮጵያን በዘር ተኮር ጭፍጨፋ ለመጠየቅ ታስቦ የነበረው ህግ መሰረዙ ይፋ ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ያደረገውን ስብሰባ መሰረት በማድረግ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለምክር ቤቱ መረጃ መላኩ ታውቋል፡፡ በመረጃውም በኢትዮጵያ “የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተካሂዷል” በሚል ሀሰተኛ ውንጀላ ኢትዮጵያን ለመጠየቅ የሚረዳና በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው ሕግ ማለትም ÷ #HR_4350 አንቀፅ6464 “Determination of Potential Genocide or Crimes Against Humanity” የሚለው ረቂቅ ህግ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ምክር ቤቱ ይፋ አድርጎል።
ታስቦ የነበረውን ህግ ለማሰረዝ በሴናተር ጂም እና በሲቪል ምክር ቤቱ መካከል አጀንዳ ሆኖ ክርክር ተደርጎበት ነበር። የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ለሴናተር ጂም ኢንሆፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማሳደር ሲል የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር እየተከተላቸው ከነበሩት መንገዶች መካከል ይህ የተለያዩ ሚዲያዎችን የሀሰት መረጃ መሰረት አድርጎ
ሲዘጋጅ የነበረው ህግ አንዱ ነበር።