loading
ካይሮ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአዲስ አበባ ደርሶኛል አለች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29፣ 2013 ካይሮ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአዲስ አበባ ደርሶኛል አለች፡፡
የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሀመድ አብደል አቲ የኢትዮጵያው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ኢንጂኔር ስለሺ በቀለ በላኩልኝ ይፋዊ ደብዳቤ ሀገራቸው በተናጠል ውሳኔዋ ፀንታ ሁለተኛውን ዙር ሙሌት መጀመሯን አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡
አብደል አቲ ለኢንጂኔር ስለሺ በጻፉት የመልስ ደብዳቤ ግብፅ የኢትዮጵያን የተናጠል ውሳኔ አጥብቃ እደምትቃወም መግለፃቸውን ኢጂፕት ቱዴይ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ድርጊት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2015 በሶስቱ ሀገራት የተፈረመውን የመርህ ስምምነትና የዓለም አቀፉን ህግ በግላጭ የጣሰ ነው ብለዋል፡፡

የግብፅ የመስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን አቋም የተፋሰሱ ሀገራት የሚጎዳና ከመጥፎ ዓላማ የመነጨ ብሎታል፡፡

ኢትዮጵያ በበኩሏ ግድቡ የኛን የሃይል ችግር የሚፈታና የውሃውን ተጋሪ ሀገራት በጎርፍ የመጥለቅለቅ ስጋት የሚቀንስ ፕሮጀክት መሆኑን አስረግጣ ተናገራለች፡፡

ሌሎችን ላለመጉዳት ማሰባችንን የሚያሳየው አንዱ ጉዳይ የክረምቱን ዝናብ ተጠቅመን ግድቡን ለመሙላት መነሳታችን ነው በማለትም አስረድታለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *