loading
በቤት ሰራተኛዋ ላይ ግፍ ስትፈፅም የቆየችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1፣ 2013  የቤት ሰራተኛዋን ከ1 ዓመት በላይ ከቤት እንዳትወጣና ምግብ በመከልከል ከፍተኛ በደል ስትፈፅም የነበረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገልጿል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲ.ኤም.ሲ አልታድ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ተጠርጣሪዋ በቤት ሰራተኛዋ ላይ ከፈፀመቻቸው አሰደቃቂ ድርጊቶች መካከል ከቤት እንዳትወጣና የፀሃይ ብርሃን እንዳታገኝ ማድረግ፣ ከፍተኛ ድብደባ መፈፀም፣ ምግብ መከልከል የሚሉት ይገኙበታል ብሏል ፖሊስ፡፡

የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሴቶችና ህፃናት ወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ኤርሚያስ ጋቸኖ እንደገለፁት ግለሰቧ በቤት ሰራተኝነት በቀጠረቻት የ20 ዓመት ወጣት ላይ የፈጸመችውን ድርጊት ያጋለጡት የቤት አከራይዋ ናቸው፡፡ የግል ተበዳይ የሆነችው ወጣት ጥሩአለም ደጉ በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረች ጊዜ ጀምሮ ለ1 አመት ከ2 ወር ያህል ከባድ የሆነ ስቃይ ሲደርስባት እንደነበር ገልፃለች፡፡

አቶ ዮሃንስ ኃ/ጊዮርጊስ የተባሉት የቤቱ አከራይ በወረቀት ተፅፎ በመስኮት የተወረወረላቸውን መልዕክት ካገኙ በኋላ በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመጠቆማቸው ነው ፖሊስ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር ያዋላት፡፡ ፖሊስ ወደ ስፍራው ሲደርስ ተጠርጣሪዋ ሰራተኛ እንደሌላት በመናገር ልትደብቃት ብትሞክርም ሰራተኛዋ ስትጮኽ ፖሊስ በመስማቱ ካለችበት ስቃይ አድኗታል መባሉን ከፖሊስ ኮሚሽን ማህበራዊ ድረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *