loading
በናይጄሪያ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 25፣ 2013 በናይጄሪያ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተሰማ:: ባለፈው ዓርብ በሰሜን ናይጄሪያ በአዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ እንዳሉ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደው የነበሩ 279 ልጃገረዶች በሰላም ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ ልጃገረዶቹ ከአጋቾቻቸው እጅ ነፃ እዲወጡ የግዛቲቱ አስተዳዳሪዎች ሰፊ ድርድር አድርገው እንደነበር ነው የተነገረው፡፡

ታጋቾቹ ነፃ ከወጡ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ ነው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እዲቀላቀሉ የተደረገው፡፡ ህፃናቱ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው ከወላጆቻቸው ጋር ሲገናኙ በደስታ ሲያነቡ ታይተዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዛምፋራ ግዛት ባለስልጣናት ከህፃናቱን እገታ ጀርባ በተደጋጋሚ በአካባቢው እንስሳትን በመዝረፍ የሚታወቁ ሽፍቶች እጅ ነበረበት ብለዋል፡፡

የእገታው ዋነኛ ዓላማም ህፃናቱን ማስያዣ አደርገው በመደራደር ገንዘብ ማግኘት ሲሆን እኛ ግን ምንም አይነት ክፍያ ሳንፈፅም ነው ህፃናቱን ያስመለስንው ብለዋል ባለስልጣናቱ፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቦኩሀራምን ጨምሮ በሰሜናዊ ናይጄሪያ የሚነቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች በህፃናት ላይ ተደጋጋሚ እገታዎችን በማድረግ በሀገሪቱ መንግስት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *