የዩኬ ሩብ ዓመታዊ ብድር ከፍተኛ ክብረወሰን አስመዘገበ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ14፣ 2012 የዩኬ ሩብ ዓመታዊ ብድር ከፍተኛ ክብረወሰን አስመዘገበ::የእንግሊዝ መንግሥት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዜጎች ላይ ከፍተኛ የፋይናንስ ጫና እያደረሰ በመሆኑ የእንግሊዝ መንግሥት ከኤፕሪል እስከ ሰኔ ወር ድረስ ብቻ የ127.9 ቢሊዮን ዩሮ ብድር አግኝቷል፡፡ አኃዙ በወጪ እና በግብር ገቢ መካከል ያለው ልዩነት ካለፈው የግብር ዓመት በሙሉ ከተበደረው 55.4 ቢሊዮን ዩሮ እጥፍ ነበር። ሆኖም በሰኔ ወር ውስጥ ከተደረገዉ ብድር አንፃር በግንቦት ወር የተገኘዉ ብድር ከ 35.5 ቢሊዮን ዩሮ በታች ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከቀድሞዉ አንፃር ተጨማሪ ቸርቻሪዎችና ሌሎች ድርጅቶች እንደገና መከፈታቸው የተዘበራረቀ እቅድን መቀነስ እና የግብር አነሳስ ጭማሪ አሳይቷል። ይሁን እንጂ የሰኔ ብድር መጠን ከፈረንጆቹ 1993 ጀምሮ የተደረገ ከፍተኘዉ ብድር መሆኑ ተገልፅዋል፡፡ ይህም ካለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር የብድር መጠኑ በ5 እጥፍ ብልጫ እንዳለዉ ታዉቋል፡፡ የሃገሪቱ ፋይናንስ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ፖል ጆንሰን ለቢቢሲ እንደገለፁት በዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ውስጥ የተደረገዉ የብድር መጠን ለአመታት ተደርጎ የማይታወቅ ከፍተኛ ነዉ ብለዋ፡፡ይህ የብድር መጠንም ምናልባትም ከአገራዊ ገቢ 15በመቶ ገደማ አለፍ ሲልም ትንሽ የበለጠ ሊሆን ይችላል ተብለሏል፡፡ ይህም ሃገሪቱ ከአንደኛው እና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውጭ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከተበደረችዉ ብድር ከፍተኛዉን ቁጥር ይይዛል፡፡