loading
ኢትዮጵያ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበረከተላት

ኢትዮጵያ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበረከተላት

የአሜሪካ ናሽናል አክርዲቴሽን ቦርድ በመባል የሚታወቀው የጥራት መመዘኛ ተቋም የኢትዮጵያ የምግብና የመድኅኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የአውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል፡፡

የተበረከተው ሰርተፍኬት  የመድኅኒት ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ እና የኮንዶም ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ በISO1725 ሁለተኛ ዙር ኦዲት በማድረግ መስፈርቶችን ሁሉ በመሟላታቸው  ሲሆን የእውቅና ሰርተፊኬት እ.ኤ.አ. እስከ መያዚያ 2021 የሚቆይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የጤና ሚኒስትሩ  ዶክተር  አሚር አማን ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉትን የመስሪያ ቤቱን አመራሮችና ሰራተኞች በጤና ሚኒስቴር ስም አመስግነዋል፡፡
በሌሎች ዘርፎችም የተጀመሩትን የጥራት ማረጋገጥ ስራዎችን ተጠናከረው እንደሚቀጥሉ ዶክተር አሚር አማን  በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *