በደቡብ አፍሪካ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር አሁንም እያሻቀበ ነው፡፡
በደቡብ አፍሪካ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር አሁንም እያሻቀበ ነው፡፡
ከ60 በላይ ዜጎችን ለህልፈት የዳረገው ይህ አደጋ በደቡባዊ እና ምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡
በኩዋዙሉ ናታል ግዛት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከመኖሪያ ቤቶች እና ከህንጻ ፍርስርስራሾች በቁፋሮ የነብስ አድን ስራቸውን እያከናወኑ ነው፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎዛ አደጋው የተከሰተበትን አከባቢ በጎበኙበት ወቅት አደጋው ሁላችንንም እንደ ሀገር የሚያስተሳስረንና ለተጎጂዎች በጋራ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
ፕሬዜዳንቱ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የነፍስ አድን ሰራተኞች ላደረጉት አፋጣኝ ምላሽ ምስጋና አቅርበው በአደጋው ከአንድ ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡
አውሎ ነፋስ የቀላቀለው ዝናብ እስካሁን ከፍ ያለ ጉዳት ያስከተለ ሲሆን፣ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማትን ማውደሙን አልጄዚራ ዘግቧል።
አብነት ታምራት