ዚነዲን ዚነዲን ተሸነፈ…
በ30ኛው ሳምንት የስፔን ላ ሊጋ ግጥሚያ በፈረንሳያዊው አሰልጣኝ ዚነደን ዚዳን የሚመራው ሪያል ማድሪድ ወደ ደቡብ ምስራቅ ጠረፍ ተጉዞ በእስታዲዮ ሜስታያ ላይ በቫሌንሲያ የ2 ለ 1 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡
ማድሪድ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛውን የላ ሊጋ ሽንፈት ያስተናገደ ሲሆን ዚዳን ዳግም ወደ ቤርናቤው ከመጣ በኋላ ደግሞ የመጀመሪያ ሽንፈት ገጥሞታል፡፡
ለቫሌንሲያ ሶስት ነጥብ እውን መሆን ጎንካሎ ጉይዴስ እና እዝኩዬል ጋራይ ጎሎችን ሲያስቆጥሩ ፤ ካሪም ቤንዜማ የሎስ ብላንኮስን የማስተዛዘኛ ጎል በጭማሪው ደቂቃ ከመረብ አገናኝቷል፡፡
አሁን ነጭ ለባሾቹ ከሊጉ መሪ ባርሴሎና ያላቸው የነጥብ ልዩነት ወደ 13 ከፍ ብሏል፡፡
ቫሌንሲያ ደግሞ ድሉን ተከትሎ ደረጃውን ወደ አምስተኛ ከፍ በማድረግ አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሄታፌ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ ተቀምጧል፡፡