ባለፈው መስከረም ከነትጥቃቸው ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የገቡ ወታደሮች ፍርዳቸው በይግባኝ ተቀነሰላቸው
ባለፈው መስከረም ከነትጥቃቸው ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የገቡ ወታደሮች ፍርዳቸው በይግባኝ ተቀነሰላቸው
ውሳኔውን ያሳለፈው በመከላከያ ፍትሕ መምርያ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው፡፡
ከ200 በላይ ኮማንዶዎች በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መግባታቸው ሲታወስ፣ 66 አባላት ግን በወታደራዊ ፍርድ ቤት የእስር ፍርድ ሲተላለፍባቸው የተቀሩት አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው በወቅቱ ተገልጾ ነበር፡፡
14 አመት የነበረው ከፍተኛው የእስር ጣሪያ ወደ 10 ዝቅ ሲደረግ፣ ዝቅተኛው የእስር ጊዜ 5 አመት ተደርጎላቸዋል ነው የተባለው፡፡
ፍርደኞቹ ከፍርድ በኋላ ከታጠቅ እስር ቤት ወደ ሸዋ ሮቢት እና ቃሊቲ መዛወራቸውን እና በሕጉ መሠረት ፍርደኞቹ የእስር ዘመናቸውን ጨርሰው ወደ ሠራዊቱ የመመለሳቸው ዕድል አናሳ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡