loading
ማንችስተር ሲቲ ወደ ሊጉ መሪነት የሚመለስበትን ጨዋታ ዛሬ ያደርጋል፡፡

የ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ትናንት የተጀመሩ ሲሆን ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ፡፡

በዛሬው ዕለት ሶስት ግጥሚያዎች በተመሳሳይ ምሽት 3፡45 የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

የጓርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲየም ከሊጉ ላለመውረድ እየታገለ የሚገኘውን የዌልሱን ካርዲፍ ሲቲ ያስተናግዳል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ሲቲ ድል የሚቀናው ከሆነ የሊጉን መሪነት ከሊቨርፑል የሚረከብ ይሆናል፡፡ በኒል ዋርኖክ የሚመራው ቡድን በግፍ በቼልሲ በተሸነፈበት የእሁዱን የጨዋታ እንቅስቃሴ ለማንችስተሩ ቡድን ላይ ሊያሳ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

ከአራቱ ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ ላለመውጣት ጥረት እያደረገ የሚገኘው ቶተንሃም ሆትስፐር አዲስ ባስገነባው ስታዲየም የመጀመሪያ ጨዋታውን ከክሪስታል ፓላስ የሚጫወት ይሆናል፡፡

አዲሱ ስታዲየም ለለንደን ከተማ ትልቅ ኩራት እንደሆነ እየተነገረለት ሲሆን ከ60 ሺ በላይ ተመልካቾችን አንቀባሮ የመያዝ አቅም አለው፡፡

የማውሪሲዮ ፖቼቲኖው ቡድን እየገጠመው ካለው ሽንፈት ለማገገም እና የቻምፒዮንስ ሊጉን ተሳትፎ ለማስጠበቅ የለንደን ተቀናቃኙን ፓላስ ማሸነፍ ይጠበቅበታል፡፡

የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ደግሞ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ከብራይተን ጋር ይጫወታል፡፡

ሰማያዊዎቹ የሚያሸንፉ ከሆነ ደረጃቸውን የሚያሻሽሉ ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *