የኦሮሞ ህዝብ እኔ ሳይሆን እኛ የሚል ነገር ነው የሚያውቀው አሉ ከንቲባ ታከለ ኡማ፡፡
የኦሮሞ ህዝብ እኔ ሳይሆን እኛ የሚል ነገር ነው የሚያውቀው አሉ ከንቲባ ታከለ ኡማ፡፡
ከንቲባዉ ይህንን የተናገሩት 29ኛው የODP የምሥረታ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረበት ወቅት ነዉ፡፡
በስነስርዓቱ ላይ ከንቲባ ታከለ እንደተናገሩት የኦሮሞ ህዝብ እኔ የሚል ነገር አያውቅም፤ እኛ የሚል ነገር ነው የሚያውቀው፤ ባህሉም አቃፊ ነው ብለዋል።
ከንቲባዉ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር አብሮ መኖርን በደንብ የሚያውቅ ህዝብ ነው ያሉ ሲሆን ፤ሞጋሳና ጉዲፈቻ ለዚህ ባህሉ ማሳያ ነው ብለዋል።
ኦዲፒ ውስጥ ስልጣን ወይም ሞት የሚል የለም ያሉት ኢንጂነር ታከለ ፤ይህንን የሚል ካለ የአባገዳን ስርዓት የማያውቅ ነው በማለት መግለጻቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል ።
በበዓሉ ላይ የእህት ድርጅት ተወካዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡