loading
ኦዚል የቱርኩን ፕሬዚዳንት የስርጌ ታዳሚ ይሁንልኝ እያለ ነው

የአርሰናሉ ጀርመናዊ ኮከብ ሜሱት ኦዚል በመጪው ክረምት ከዕጮኛው አሚኔ ጉልስ ጋር ለሚፈፅመው የጋብቻ ስነ ስርዓት የደስታዬ ተካፋይ ይሁኑ በማለት፤ ለቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን የሰርጉን የጥሪ ካርድ ባለፈው ሳምንት ከዕጮኛው ጋር በመሆን በአካል ተገኝቶ አድርሷል፡፡

ኦዚል ለኤርዶሃን የጥሪ ካርድ ማድረሱን ተከትሎ፤ የአንሄላ ሜርክል የፅ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ በጀርመናውያኑ ዘንድ ተቃውሞ እያስተናገደ ይገኛል፡፡

የ30 ዓመቱ ተጨዋች የወላጆቹ የዘር ግንድ ከቱርክ የሚመዘዝ ሲሆን ከዓለም ዋንጫው ዋዜማ ግንቦት ወር ውስጥ ለንደን ላይ ከኤርዶሃን ጋር ፎቶ መነሳቱን ተከትሎ በውድድሩ ለሀገሩ ስለሚኖረው ታማኝነት ብዙዎቹ ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓቸዋል፡፡

የጀርመናውያኑ ጭቅጭቅ ሲታክተው በ92 ያህል ጨዋታዎች ካገለገለ በኋላ፤ ለሚነሳበት የዘረኝነት ትችት የሀገሪቱ የእግር ኳስ ባለስልጣናት ከጎኔ አልቆሙም በማለት፤ ከዚህ በኋላ ነጩን ማሊያ አልብስም ሲል ሐምሌ ወር ላይ በድንገት ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

አሁን ደግሞ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ጋር ያለው ፍቅር ከፍ ብሎ በሰርጉ ቀን ምስክር ሁነው እንዲታደሙ፤ ቤተመንግስት ድረስ በመጓዝ የጥሪ ካርዱን በክብር ማድረሱ ኦዚል ላይ የሚሰነዘረው ትችት እና ጩኽት እንዲንር አድርጎበታል፡፡

ይሄንን መረጃ የጀርመኑ ተነባቢ ጋዜጣ ቢልድ ይዞት የወጣ ሲሆን የቀድሞዋ የሚስ ቱርክ አሸናፊ እና የአሁኗ የ25 ዓመት ሞዴል አሚኔ ጉልስ ከወደፊት ባለቤቷ ጋር በመሆን ለፕሬዚዳንት ኤርዶሃን የጥሪ ካርዱን ሲያቀብሉ የሚያሳይ ፎቶ ይዞ ወጥቷል፡፡

ጀርመን በአንካራ ላይ ያላት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍ እያለ ባለበት ወቅት የኦዚል እና ቱርክ ግንኙነት ከፍ ማለት በጀርመን ፖለቲከኞች ዘንድ ጉዳዩን ፖለቲካዊ አንድምታ አላብሰውታል፡፡

ኢዚል እና ጉልሴ የፍቅር ግንኙነታቸው 2017 ላይ የጀመረ ሲሆን ሰኔ 2018 ጥምረታቸውን ከፍ በማድረግ ቀለበት አስረዋል፤ አሁን ደግሞ ከወራት በኋላ ክረምት ላይ ጋብቻቸውን ይናፍቃሉ፡፡

እውን ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይብ ኤርዶጋን በሰርጉ ስነ ስርዓት ታዳሚ ይሆኑ ይሆን…?

የመረጃው ምንጭ ቴሌግራፍ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *