loading
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-8 ማክስ የተሰኙት አውሮፕላኖቹ ከበረራ አገልግሎት እንዲወጡ መወሰኑን አስታወቀ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-8 ማክስ የተሰኙት አውሮፕላኖቹ ከበረራ አገልግሎት እንዲወጡ መወሰኑን አስታወቀ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫው ነው አውሮፕላኖቹን ላልተወሰነ ጊዜ ከበረራ ማስወጣቱን ያስታወቀው።

አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰውም በትናንትናው እለት ቦይንግ 737-8 ማክስ በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የደረሰበትን የመከስከስ አደጋ ተከትሎ መሆኑንም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የአደጋው መንስኤ ተጣርቶ እስኪታወቅ ድረስ ለመንገደኞች ደህንነትና ጥንቃቄ ሲባል ቦይንግ 737-8 ማክስ የተሰኙት አውሮፕላኖቹን በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከበረራ አገልግሎት እንዲወጡ መወሰኑን ገልጿል።

አየር መንገዱ ቦይንግ 737-8 ማክስ የተሰኙት አምስት አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን፥ በትናንትናው እለት የተከሰከሰውም ከአራት ወራት በፊት የተረከበው 4ኛው አውሮፕላኑ ነበር።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *