ደቡብ አፍሪካ በነጭ ገበሬዎች የተያዘ መሬቷን ለማስመለስ ህገ መንግስቷን ልታሻሽል ነው፡፡
አዲሱ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲርሊ ራፋሞሳ ፓርቲያቸው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ኤ ኤን ሲ ሀሳቡ ገቢራዊ እዲሆን ቅድሚያውን መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡
ሩሲያ ቱደይ እንደዘገበው የህገ መንግስቱ መሻሻል ያለምንም የካሳ ክፍያ በነጭ ገበሬዎች የተወሰደው መሬት ለሀገሬው ህዝብ እንዲመለስ መንገድ ይጠርጋል ነው የተባለው፡፡
ፕሬዝዳንቱ ከአሁን በፊት በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በሀገሪቱ ፍትሀዊ የመሬት ክፍፍል እንዲኖር በማሰብ እንጂ ማንንም ለማጥቃት ዓላማ የለንም፣ ሁሉንም አካል ያሳተፈ ውይይት እናደርደጋለን ማለቸታው ይታወቃል፡፡