ከአፍሪካ ህብረት መስራች መሪዎች አንዱ የሆኑት የቀድሞ የኢትዮጵያ ንጉሰ ቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሀውልት ተገነባላቸው
ከአፍሪካ ህብረት መስራች መሪዎች አንዱ የሆኑት የቀድሞ የኢትዮጵያ ንጉሰ ቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሀውልት ተገነባላቸው ።
ሀውልቱ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቅጥር ግቢ ውስጥ የቆመ ሲሆን የሃውልቱ ዲዛይን እና ግንባታ የተከናወነውም በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት መሆኑ ተነግሯል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አቶ ነብያት ጌታቸው እንዳሉት ሃውልቱ የተገነባው እ.ኢ.አ በ 2017 የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ወቅት ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ለአፍሪካ ፀረ- ቅኝ ግዛት ትግል ያደረጉትን አስተዋፆ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀውልት እንዲቆምላቸው በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ነው።