የእስያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ
የእስያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ
17ኛው የእስያ ዋንጫ በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አዘጋጅነት ከጥር 5/2019 ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በ24 ቡድኖች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ዛሬ አንድ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሚከናወን ሲሆን በሀዛ ቢን ዛይድ ስታዲየም 11፡00 ሲል በኢራን እና ጃፓን መካከል ይከናወናል፡፡
በሩብ ፍፃሜው ኢራን ቻይናን 3 ለ 0 እንዲሁም ጃፓን ቬትናምን 1 ለ 0 በመርታት ነው ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀሉት፡፡
ነገ ደግሞ ኳታር በመሀመድ ቢን ዛይድ ስታዲየም ከአዘጋጇ የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ጋር በ11፡00 ይጫወታሉ፡፡
ኳታር የሰን ሁንግ ሚንን ሀገር ደቡብ ኮሪያ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች አውስትራሊያን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈው በፖለቲካው ያለውን ቁርሾ ወደ ጎን ብለው ይሄንን ፍልሚያ ያከናውናሉ፡፡
የውድድሩን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት የኳታሩ አጥቂ አልሞኤዝ አሊ በ7 ጎሎች እየመራ ይገኛል፡፡
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎቹ አሸናፊዎች በመጭው የካቲት 1/2019 አቡ ዳቢ ላይ በተገማሸረው የዛይድ ስፖርትስ ሲቲ ስታዲየም ይፋለማሉ፡፡