loading
ሺሴኪዲ ለእርቅ እና ሰላምን ቅድሚያ እሰጣለሁ አሉ፡፡

ሺሴኪዲ ለእርቅ እና ሰላምን ቅድሚያ እሰጣለሁ አሉ፡፡

በዲሞክራት ኮንጎ ታሪክ በሰላማዊ መንገድ ወደ ስልጣን የመጡት ፊሊክስ ሺሴኪዲ ቃለ መሀላ ሲፈፅሙ ለህዝባቸው ሶስት ነገሮችን ለማሳካት ቃል ገብተዋል፡፡

አዲሱ ፕሬዝዳንት ቅድሚያ ሰጥቸ እሰራባቸዋለሁ ካሏቸው እቅዶቻቸው መካከል የመጀመሪያው በሀገሪቱ እርቅ እና ሰላምን ማስፈን ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ወቅት ከእንግዲህ ኮንጎ የእርቅ ምድር ናት በማለት የከሰሷቸውን ተቀናቃኛቸውን ማርቲን ፋዩሉን ጭምር አድናቆጣቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡

ፋዩሉ ከሮይተርስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ  ሺሴኪዲ የተመረጠ ፕሬዝዳንት ሳይሆን በጆሴፍ ካቢላ የተሾመ ፖለቲከኛ ነው ቢሏቸውም ሺሴኪዲ ግን እሱ የጎንጎ ህዝብ ወታደር ነው በማለት አሞካሽተዋቸዋል፡፡

ሌላው የሽሴኪዲ አጀንዳ በሳቸው ዘመነ መንግስት ሰብዓዊ መብት እንዳይጣስ ጠንክሮ መስራት ነው ፡፡

እኔ በሰልጣን በምቆይባቸው ዓመታት ሁሉም ዜጎች አድልዎ ሳይፈፀምባቸው እና  መሰረታዊ መብቶቻቸው ተከብረውላቸው እንዲኖሩ ዋስትና  እሰጣለሁ ብለዋል፡፡

ሺሴኪዲ በመጨረሻም ጠንካራዋን ኮንጎን ለመገንባት በጋራ እንነሳ የሚል መልእክት ለደጋፊዎቻቸው አስተላልፈዋል፡፡

ይህን የምናደርገው ሰላም እና መረጋጋትን በማስፈን ሁላችንም ሀገራችንን በጋራ ማልማት ስንችል ብቻ ነው በማለትም ህዝቡን ለመልካም ነገር የሚያነሳሳ ንግግር አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት በድንገት ህመም ተሰምቷቸው ንግግራቸው ለ12 ደቂቃዎቸድ ያህል ተቋርጦ ነበር ተብሏል፡፡

ትርጉም በመንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *