ተቋሙ ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ ደንበኞቹ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በባንክ እንዲከፍሉ የሚያስችል የውል ስምምነት ሊያደርግ ነው
ተቋሙ ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ ደንበኞቹ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በባንክ እንዲከፍሉ የሚያስችል የውል ስምምነት ሊያደርግ ነው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 27000 የሚሆኑ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀሙ ደንበኞቹ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ደንበኞቹ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በባንክ እንዲከፍሉ የሚያስችል የውል ስምምነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይፈራረማል፡፡
የስምምነት ሥነ ስርዓቱ ዛሬ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የሁለቱ ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች በተገኙበት የሚከናወን እንደሆነ ከተቋሙ ድረ -ገፅ ያገኝነው መረጃ ይጠቁማል::