የፈረንሳይ አመፅ እንደገና አገርሽቶበታል፡፡
የፈረንሳይ አመፅ እንደገና አገርሽቶበታል፡፡
ቢጫ ሰደርያዎችን ለብሰው ጎዳናዎችን ሲያጥለቀልቁ የከረሙት ፈረንሳዊያን ትንሽ ንዴታቸው በርዶ ወደ የቤታቸው ገብተው ነበር፡፡
ሰሞኑን ግን እንደገና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች ዳግም ጎዳና ወጥተው ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለአስር ተከታታይ ሳምንታት በመላው ፈረንሳይ የተቀጣጠለውን አመፅ ለማብረድ ፍላጎ ታቸውን ለማሟላት የሚያስችል ውይይት አድርጓል፡፡
በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ለአመፅ ከወጡት ሰዎች መካከል ከ20 በላይ የሚሆኑት በፖሊስ ተይዘው ማረፊያ ቤት ገብተዋል ተብሏል፡፡
ቀን ላይ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ይገልፁ የነበሩ ሰልፈኞች አመሻሽ ላይ ፖሊስ እንዲበተኑ ከባድ ግፊት ያለው ውሀ እና አስለቃሽ ጪስ መጠቀም ሲጀምር ወደ ብጥብጥ ተቀይሯል ነው የተባለው፡፡
ፓሪስን ጨምሮ ባለፈው ሳምንት በጠቅላለ ሀገሪቱ 84 ሺህ ነዋሪዎች በተቃውሞ ሰልፉ የተሳተፉ ሲሆን መንግስት አመፁን ለመቆጣር 80 ሺህ የፀጥታ ሀይሎችን አሰማርቷል፡፡
በፈረንሳይ አመፁ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ አስር ሰዎች ሞተዋል፤ 2 ሺህ የሚሆኑት ቆስለዋል፣ 6 ሺህ የአመፁ ተካፋዮች ደግሞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በነዳጅ ዋጋ ጭማሬ ሳቢያ የተቀሰቀሰው የፈረንሳይ አመፅ የኋላ ኋላ ኢማኑኤል ማክሮን ከስልጣን ይውረዱ ወደሚል ጥያቄ ተሸጋግሯል፡፡