ግብጻዊው ጸሀፊ ግብጽ ወደ ንጉሳዊ የአገዛዝ ዘመን እንድትመለስ ጥያቄ አቀረበ፡፡
ዳንድራዊ አል ሀዋሪ የተባለው ግብጻዊ ደራሲ ሀገሪቱ ወደ ቀድሞው ስርዓት ስትመለስ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ደግሞ ንጉስ ሆነው መሰየም አለባቸው የሚል ሃሳብም አቅርቧል፡፡
የደራሲውን ሀሳብ ብዙዎች አውግዘውታል፣ በርካቶችንም ለብስጭት ዳርጓል ይላል የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ፡፡
ከአስተያየት ሰጭዎቹ መካክል እንዲህ አይነቱ ሀሳብ ግብዝነት የተሞላበትና ሀገሪቱን የማይጠቅም ነው በማለትም አጣጥለውታል፡፡