በአማራ ክልል የሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
በአማራ ክልል የሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ አህመድ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል ሠላማዊ ሆኖ እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
በዓሉ በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ከተለመደው ጊዜ የተለየ እና የተጠናከረ ጥበቃ ይደረጋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላትን ለመቆጣጠር የወንጀል ክትትል አባላት መሰማራታቸውንና አቅማቸው ከፍ እንዲል መደረጉንም ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ ተናግረዋል፡፡
እንደ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘገባ በጥምቀት በዓል የውጭ ሀገራት ጐብኝዎች ቁጥር እንደሚጨምር ረዳት ኮሚሽነሩ ተናግረው፤ ጐብኝዎች በሚጓጓዙበትና በሚያርፉበት አካባቢ ልዩ ጥበቃ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
በዘንድሮው የጥምቀት በዓል 15 ሺህ የውጭ ሀገራት ዜጎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡