loading
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ

ኢንጂነር ታከለ ኡማቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ  ከተማ ምክትል ከንቲባ  ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ።

ምክትል ከንቲባው በቤቶች ልማት ላይ ተሳታፊ ከሆኑ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር በያዝነው በጀት ዓመት በሚተላለፉ 134 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው በመድረኩ ላይም  ከሁለቱም ወገን ያለውን ችግር በመፍታት  በአፋጣኝ ቤቶቹን ለተጠቃሚዎች ማድረስ እንደሚገባው ገልፀዋል።
ይህ እንዲሆንም በመንግስት በኩል ያለውን የግብዓት ፣ የፋይናንስ እና ተያያዥ አስተዳደራዊ ችግሮችን በሙሉ ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ከምን ጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ ባለፈም የህንፃ ተቋራጮች እና አማካሪዎች በግንባታ ላይ የሚገኙ ቤቶችን  በአፋጣኝ አጠናቅቀው ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፉ አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን የቤት ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ የቤት ልማት አካሄድ እንደሚከተል ማሳወቃቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *