37ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል፡፡
37ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል፡፡
ስብሰባው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን 55 የአባል ሀገራቱ ተወካይ አምባሳደሮች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡
ጉባኤተኞቹ በስደት ተመላሾች እና በአህጉሪቱ እየተበራከተ ያለውን የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ በትኩረት ይመክራሉ ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ስብሰባው ሲጠናቀቅ በ32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የሚቀርብ አጀንዳ እንደሚያዘጋጁም ይጠበቃል።
አጀንዳው በወሩ መጨረሻ በሚካሄደው 34ኛው የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ ቀርቦ በስራ አስፈጻሚዎቹ ከጸደቀ በኋላ ለመሪዎች ጉባኤ ይቀርባል ተብሏል።
ከአፍሪካ ህብረት ድረገፅ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በቀጣዩ ወር ይካሄዳል።