loading
የካራባዎ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ

የካራባዎ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ

የእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ ካፕ ወይንም በስፖንሰር አድራጊው ድርጅት ካራባዎ የሚጠራው ይህ የዋንጫ ውድድር የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያዎች ዛሬ እና ነገ ይከናወናሉ፡፡

ዛሬ በለንደን ደርቢ ቶተንሃም ሆትስፐር በዊምብሌ ቼልሲን ምሽት 5፡00 ሲል ያስተናግዳል፡፡ ለማውሪሲዮ ፖቼቲኖው ቡድን በኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ሉካስ ሞራ እና ቪክተር ዋንያማ እንዲሁም ኢሪክ ዳየር ግልጋሎት አይሰጡም ተብሏል፡፡

በማውሪዚዮ ሳሪ በኩል ደግሞ ጠንካራ አሰላለፍ ይዘው እንደሚገቡ እየተነገረ ሲሆን  ፔድሮ፣ ኦሊቪዬ ጅሩ እና ዊሊያን ከጉዳት ተመልሰዋል ተብሏል፡፡ አማካዩ ማቲዎ ኮቫችችም ቢሆን ከህምም እንዳገገመ ቢነገርም ሩበን ሎፍተስ ቺክ ግን በጀርባ ህመም ከጨዋታ ውጭ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ቼልሲ በሜዳው ኖቲንግሃም ፎረስትን በኤፍ ኤ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ 2 ለ 0 ድል ሲያደርግ ቁልፍ ሚና የነበረው የ18 ዓመቱ የክንፍ መስመር ተሰላፊ ተጫዋች ካሉም ሁድሰን ኦዶይ በምሽቱ ጨዋታ ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ነገ የፔፕ ጓርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲየም ቡርቶን አልቢዮንን ያስተናግዳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *