loading
ኪም ጆንግ ኡን አሜሪካን ባስጠነቀቁ ማግስት ወደ ቻይና አቅንተዋል

ኪም ጆንግ ኡን አሜሪካን ባስጠነቀቁ ማግስት ወደ ቻይና አቅንተዋል

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ በተረደገላቸው ግብዣ ለአራተኛ ጊዜ ነው ቤጂንግ የገቡት ተብሏል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ በቻይና የሶስት ቀናት ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን ስለ ጉብኝታቸው ዓላማ ግን የተነገረ ማብራሪያ የለም፡፡

ይሁን እንጂ ቤጂንግ የፒዮንያንግ ሁነኛ የንግድ እና የዲፕሎማሲ አጋር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ይህን ሁኔታ ለማጠናር ይሆናል የሚሉ በርካቶች ናቸው፡

አንዳንዶቹ ደግሞ ኪም ወደ ቻይና ያመሩት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት በሚደራደሩበት ወቅት በመሆኑ አንዳች ምክር ለመጠየቅ ይሆናል ይላሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከኪም ጋር የሚገናኙበትን ቀን እና ቦታ የሚያሳውቁበት ጊዜ ሩቅ  እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ መንግስት በበኩሉ የኪም ቻይና መገኘት በኮሪያን ልሳነ ምድር ከኒውክሌር ስጋት ነፃ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብሏል፡፡

ዘ ቴሌግራፍ በዘገባው እንዳስነበበው ኪም በቤጂንግ ቆይታቸው ዋሽንግተን በፒዮንግያንግ ላይ የጣለችውን ማእቀብ በተመለከተ ከሺ ጂንፒንግ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ አሜሪካ በገባችው ቃል መሰረት የጣለችብንን ማእቀብ የማታነሳ ከሆነ አማራጭ መንገዶችን እንደምንከተል ትወቅ ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *