loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደደቢት የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደደቢት የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል
በ9ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ዛሬ በክልል እና አዲስ አበባ ስታዲየሞች ሶስት ያህል ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡
በትግራይ ስታዲየም የደቡቡን ወላይታ ድቻ ያስተናገደው ደደቢት 1 ለ 0 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል መቀዳጀት ችሏል፡፡ ደደቢት ሶስት ነጥብ እንዲያሳካ ያገዘችውን የድል ግብ ማስቆጠር የቻለው ደግሞ የዓብስራ ተስፋዬ ነው፡፡ ደደቢት እስካሁን ባደረጋቸው ስድስት የሊጉ ግጥሚያዎች ውስጥ ነጥብ ማግኘት የቻለው በዚህ ጨዋታ ሲሆን በሶስት ነጥቦችና ሰባት የግብ ዕዳ፤ ሶስት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት የሊጉ ግርጌ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ድሬዳዋ ላይ ደግሞ ድሬዳዋ ከነማ ባህር ዳር ከነማን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል፡፡ ለምስራቁ ቡድን የድል ግቦቹን ሀብታሙ ወልዴ እና ኢታሙና ኬይሙኔ ሲያስቆጥሩ ለእንግዳው ባህር ዳር ፍቃዱ ወርቁ ብቸኛዋን ከሽንፈት ያልታገች ግብ አስገኝቷል፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ የትግራዩን ስሑል ሽረ ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ አጥቂው አቡበከር ነስሩ ባስቆጠራት ብቸኛ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፤ ቡና ባለፉት አራት የሊጉ ጨዋታዎች ውስጥ በሶስቱ ድል ሲያደርግ ሁሉንም ግጥሚያዎች በአቡበከር ነስሩ የፍፁም ቅጣት ምት አንድ ጎል እያሸነፈ ነው፡፡
ቡናማዎቹ ድሉን ተከትሎ የደረጃ ሰንጠራዡን በ18 ነጥብ መምራታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ነገ የሊጉ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ፤ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ስታዲየም ፋሲል ከነማን ያስተናግዳል፤ ሰኞ በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ስታዲየም ሀዋሳ ከነማ ከ ጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም ትግራይ ስታዲየም ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከ ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 9፡00 ግጥሚያቸውን ያደርጋሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *