loading
በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ መሰራት ያለባቸውን ተግባራት ለማከናወን ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቅቄአለው ብሏል።

ኤጀንሲውን መዋቅር እና የህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን ተናግሯል።

ኤጀንሲውን በሰው ሃይል የማደራጀት እና በስፋት ወደ ስራ ማስገባት እንቅስቃሴ እንደሚደረግም ተነግሯል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደተናገሩት ኤጀንሲው ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ይሰራል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ በዋናነት የዲያስፖራ ማህበር ልማት፣በመዋዕለ ነዋይ ፍሰት፣በእውቀት ሽግግር፣በበጎ አድራጎት፣በሀብት ማሰባሰብ እንዲሁም በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን መብት በማስጠበቅ ላይ ያተኩራል።

ኤጀንሲው በቅርቡም በዳያስፖራው ማህበረሰብና በባለድርሻ አካላት በግልፅ ታውቆ ስራውን በይፋ ለመጀመር የመክፈቻና የትውውቅ መርሃ ግብር እያዘጋጀ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *