ሊቨርፑል ለማንችስተር ሲቲ እጅ ሰጥቷል
ሊቨርፑል ለማንችስተር ሲቲ እጅ ሰጥቷል
ቀያዬቹ ያለመሸነፍ ጉዟቸው በሲቲ ተገትቷል
ተጠባቂው የ21ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ በማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል መካከል ተካሄዶ ባለሜዳዉ ቡድን ሲቲ የ 2 ለ 1ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል ።
የማ.ሲቲን ጎሎች ኩን አጉዌሮ እና ሊሮይ ሳኔ ሲያስቆጥሩ፤ ሮቤርቶ ፊርሚኖ የቀያዮቹን ከሽንፈት ያልታደገች ጎል ከመረብ አዋህዷል ።
በየርገን ክሎፕ የሚመራው የመርሲ ሳይዱ ቡድን ፤ ለ20 የሊጉ ጨዋታዎች ያህል አስቀጥሎት የነበረውን ያለመሸነፍ ግስጋሴ በመጨረሻ በፔፕ ጓርዲዮላ ቡድን ተገትቷል ። እስከዚህ ሽንፈት ድረስ ሊቨርፑል በሊጉ ያልተረታ ብቸኛው ቡድን ነበር ።
የሊቨርፑልን ሽንፈት ተከትሎ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት ከሰባት ወደ አራት ዝቅ ብሏል ።
ሊጉን ሊቨርፑል በ54 ነጥብ ሲመራ ፤ ሲቲ በ50 ይከተላል ፤ ቶተንሃም በ48 ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።