ሞቃዲሾ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለ ስልጣን ከሀገሯ እንዲወጡ ትእዛዝ ሰጠች
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በድርጅቱ የሶማሊያ ልዩ ልኡክ ኒኮላስ ሀይሶም ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የምናደርገው በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ በመግባታቸው ነው ብሏል፡፡
ልዩ ተወካዩ የቀድሞው የአልሸባብ ቃል አቀባይ ሸይክ ሙክታር ሮቦውን መታሰር ጨምሮ ሌሎች የጥትታ ጉዳዮችን አስመልክተው ተደጋጋሚ ደብዳቤዎችን በመፃፍ የስልጣን ገደባቸውን አልፈዋል ብሏል መግለጫው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሶማሊያ ከእርስበርስ ጦርነት ወጥታ የተረጋጋች ሀገር እድትሆን ብዙ ጥረት ያደረገ ቢሆንም በሉዓላዊነቷ ግን አትደራርም የሚል መግለጫ ነው የሀገሪቱ መንግስት የሰጠው፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ሀይሶም ተቋሙ በሶማሊያ ካለው ተልእኮ ውጭ የሆነ ተግባር ላያ ተሰማርተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የሶማሊያ የሀገር ውስጥ ደህንነት ተቋም ሮቦው የታሰረው በአንድ በኩል ለፕሬዝዳንትነት እወዳደራለሁ እያለ በሌላ በኩል ደግሞ የጦር መሳሪያ እና ተዋጊ ሚሻዎችን ወደ ባይዱዋ አምጥጧል በሚል ጥርጣሬ ነው ብሏል፡፡
የግለሰቡ መታሰር በደጋፊዎቹ እና በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ምንያት መሆኑም ተነግሯል፡፡
ሙክታር ሮቦው ዳግም በሽብር ተግባር ላለመሰማራት እና በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካዊ ትግል ለማድረግ በፈረንጆቹ 2017 በይፋ መናገሩ ይታወሳል፡፡