የአፍሪካ ልማት ባንክ በፈጠራና በኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ድጋፍ ሊያደርግ ነው
የአፍሪካ ልማት ባንክ የሳይንስ እና ቴክሎኖጂ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በመርህ በመደገፍ የአፍሪካ ትምህርት ፈንድ በሚል እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል፡፡
ባንኩ በአፍሪካ ባለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የበጀት ጉድለት በመሙላትና ተቋማት ውጤታማ ለማድረግ ለአፍሪካ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ጽኑ ፍላጎት እንዳለው በማላዊ በተካሄደው የሳይንስ እና ቴክሎኖጂ ስብሰባ አስታውቋል፡፡
በባንኩ የትምህርትና የክህሎት ልማት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሄንደሬና ዶቦራ እንደገለጹት በትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎኖጂ እና በፈጠራ ላይ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት በማሳደግ የአህጉሩን የሰው ሃይል ብቃት መጨመር እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ የትምህርት ፈንድ በአፍሪካ የትምህርት ጉድለት በመሙላት ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡