loading
የአሜሪካ መከላከያ በኢራቅና በሶሪያ በርካታ ሲቪል ሰዎችን መግደሉን አመነ

 

አሜሪካና አጋሮቿ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከነሐሴ 2014 እስካስለፈው ወር መጨረሻ ድረስ የዳኢሽ ሚሊሻዎች ጦር ሰፈሮች ናቸው ባሏቸው ስፍራዎች ላይ 31 ሺህ 406 ድብደባዎችን አካሂደዋል፡፡

ፕሬስ ቴሌቭዥን  ሰሞኑን የወጣ ሪፖርትን ጠቅሶ እንደዘገበው በነዚህ ጥቃቶች  በሽዎች የሚቆጠሩ ሲቪል ሰዎች መገደላቸው ይፋ ሆኗል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሀይልም በጥምር ሀይሉ ፀረ ሽብር ኦፕሬሽኖች ቁጥራቸው 1 ሺህ 139 የሚደርስ ሲቪል ሰዎች በስህተት መገደላቸውን አምኗል ነው የተባለው፡፡

አሜሪካ በነዚህ ፀረ ዳኢሽ  ዘመቻዎች ያሰበችውን ዓላማ ከማሳካት ይልቅ በንፁሀን ዜጎች ላይ ያደረሰችው ጉዳት አመዝኖ ታይቷል በሚል ትታማለች፡፡

ዋሽንግተን እና አግጋሮቿ በኢራቅም ይሁን በሶሪያ ሽብርተኝነትን አጠፋለሁ ብላ የጀመረችው ዘመቻ ለሀገሮቹም ለራሷም ትርፍ አላስገኘም የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡

 

ምክንያታቸው ደግሞ በነዚህ ሀገራት በብዙ ሲቪል ዜጎች ላይ አደጋ ከመድረሱም በተጨማሪ አሜሪካን ለመበቀል አክራሪ ሽብርተኛ ቡድኖች በየቦታው እንዲፈጠሩ በር ከፍታለች የሚል ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከሶሪያ 20 ሽህ ወታደሮቻቸውን እንደሚያስወጡ ቃል የገቡ ቢሆንም ወታደሮቹ ሊዘገዩ እንደሚችሉ ፍንጮች ተሰምተዋል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *