ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሰው ሀይል ትብብር መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
በሁለቱ ሀገራት መካከል ድርድር ሲካሄድበት የቆየው የሰው ሀይል ትብብር መግባቢያ ሰነድ በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሰው ሀብትና ኤምሬታይዜሽን ሚኒስትር ናስር ቢን ታኒ አል ሀምሊ ተፈርሟል፡፡
እንደ ሰራተኛና ማህበረዊ ጉዳይ ገለፃ ስምምነቱ ወደተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለስራ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ህጋዊ መንገድን ተከትለው እንዲወጡ ያስችላል፡፡
ይህ ትልቅ ግምት የተሰጠው ስምምነት በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ ይሆናል፡፡