የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አቶ አድጎ አምሳያን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አቶ አድጎ አምሳያን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
አርትሰ ታህሳስ 19 2011
የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ትላንት ባካሄደው ስብሰባ አቶ አድጎ አምሳያን ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠው የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ አበራ ባየታ ያስገቡትን የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀብሎ ነው፡፡ማዕከላዊ ኮሚቴው የተጓደሉ ሶስት የስራ አስፈፃሚ አባላትን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ወደ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴነት ከፍ አድርጓል።
አዲሱ ሊቀመንበር ለህዝብ እና ለድርጅቱ መርሆች ቅድሚያ እሰጣለሁ ብለዋል።
ከማዕከላዊ ኮሚቴው ጋር በመደጋገፍም እንችላለን ነው ያሉት፡፡
በፍላጎታቸው ሃላፊነታቸውን ለለቀቁት የቀድሞው የቤጉህዴፓ ሊቀመንበር አቶ አበራ ባዬታ አክብሮታቸውን ጠቅሰው የርሳቸው ድርጊት ለሌሎች አባላት በአርአያነት የሚጠቀስ እንደሆነ መናገራቸው ከኢዜአ ያገኘነው ተጨማሪ መረጃ ያመለክታል።