የአብዴፓ 7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የፕሬዚዲየም አባላቱን መረጠ
የአብዴፓ 7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የፕሬዚዲየም አባላቱን መረጠ
አርትስ 25/03/2011
የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/ በ7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ፤7 የፕሬዚዲየም አባላቱን የመረጠ ሲሆን አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድርን ሰብሳቢ ፣ኢንጂነር አይሻ መሃመድን ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።
የአብዴፓ ሊቀመንበር ሃጂ ስዩም አወል በጉባዔው መክፈቻ እንደተናገሩት ስትራቴጂክ አመራር፣ የውስጥ ድርጅታዊ ዴሞክራሲ፣ የህግ የበላይነት፣ የተደራጀ ሌብነት እንዲሁም የግልና የቡድን የስልጣን ሽኩቻዎች ድርጅቱን በተለያዩ ጊዜያት የተፈታተኑት ነገሮች እንደነበሩ አንስተዋል።
በጉባዔው መክፈቻ ኢህአዴግን ጨምሮ የኦዴፓ፣ ህወሃትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ተወካዮች የድጋፍ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በቆይታውም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በመገምገም፥ ነባር የድርጅቱን አባላትንም በክብር ይሸኛል ተብሎ ይጠበቃል።
በሚሸኙ አባላት ምትክም ሴቶችን ያሳተፈ፣ ወጣትና የተማረ ኃይልን ወደ አመራርነት በማምጣት የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲጠናከር ይደረጋል ተብሏል።
ፋና እንደዘገበዉ በድርጅታዊ ጉባዔው 700 አባላት የታደሙ ሲሆን 594ቱ በድምፅ የሚሳተፉ ናቸው።