ህንድ የዓለማችንን ረዥም ሃውልት አስመረቀች
አርትስ 21/02/2011
ህንድ በቁመቱ በዓለማችን ላይ ካሉ እና ረዣዣም የሚባሉ ሃውልቶችን ያስናቀ የተባለለትን ሀውልት ግንባታን አጠናቃ ይፋ አድርጋለች፡፡
በ29 ነጥብ 9 ቢሊየን የህንድ ሩፒ ወይም በ430 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባው ረዥሙ ሃውልት ቁመቱ 182 ሜትር ወይም 600 ጫማ ከፍታ ያለው ሲሆን 67ሺህ ቶን ሚመዝን እና 1 ሺህ 800 ቶን ነሃስ ጥቅም ላይ ውሎ በነሃስ ቅብ የታነፀ መሆኑም ተነግሯል፡፡
በህንድ ጉጅራት በተሰኘቸው ግዛት የተገነባው ሀውልቱ በህንድ የነፃነት ትግል ታሪክ ውስጥ በጀግንነታቸው የሚነሱት የሳርዳር ቫላብባሂ ፓቴል መታሰቢያነት ነው የተሰራው፡፡
ሀውልቱን መርቀው የከፈቱት የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ሀውልቱ የአንድነት ምልክት እንደሆነ እና ለቱሪስት መስህብነትእንደሚያገለግልም ተናግረዋል
በቻይና የተያዘውን የሀውልት ቁመት ክብረወሰን ተቀብሎ ሀውልቱ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ረዥሙ ሃውልት እንደተባለ በበሲ በዘገባው ጠቁሟል፡፡
እስከአሁን የአለማችን የረዥሙ ሃውልት ክብረወሰን የቻይናው የቡድሃ ሃውልት በ 128 ሜትር ይዞ የቆየ ሲሆን ፣ የጃፓኑ በ 120 ሜትር፣ የአሜሪካው ሃውልት በ98 ሜትር እና የብራዚሉ ክራይስት ዘሬዲሚር ሃውልት በ 38 መትር የሚከተሉ ሃውልቶች ናቸው፡፡