loading
ኢትዮጵያዊዉ ወጣት ለህትመት አገልግሎት የሚዉል ሮቦት ሰራ

ኢትዮጵያዊዉ ወጣት ለህትመት አገልግሎት የሚዉል ሮቦት ሰራ

አርትስ 21/02/2011

ሮቦቱ  ከሰው እጅ ንክኪ ነፃ የሆነ እና በኮምፒውተር ትዕዛዝ ብቻ የሚከናወን የማተሚያ ማሽን ሲሆን የተለያየ ቅርፅ ያለቸውን የህትመት ውጤቶች በቀላሉ የሚያትም ነው፡፡

ማሽኑ በሃገር ውስጥ ከሚገኙ ልዩ ልዩ ቁሶች ተዋቅሮ የተሰራ ሲሆን ለመኪና መለዋወጫ የሚሆኑ ቅርፆችን ከማውጣት ጀምሮ በአጥንት ስብራት የተጎዱ ሰዎች በመተኪያነት የሚገለገሉበትን አርተፊሻልብረት ለመስራትም የሚያስችል ነው፡፡
የ 21 ዓመቱ  ዋሲሁን ተፈራ  በአሁን ወቅት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ የኤሌክትሮ ሜካኒካል የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ሲሆን የመረጠው የትምህርት ዘርፍም እንደሮቦትያሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አይነቶችን ለመፍጠር እንዳገዘው ይገልፃል፡፡

ወጣቱ  ከዚህ በፊት አረቄ በማውጣት ለተሰማሩ እናቶች አድካሚ የነበረውን አሰራር በሚያቀል ሁኔታ ከሲሚንቶ ግብዓት በተሰራ ምድጃ እንዲገለገሉ የሚያስችል ፈጠራ  ሰርቷል፡፡

 ዋሲሁን ከዚህ ስራው በተጨማሪ ምግቦችን እና ትኩስ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ማፍላት የሚችል እስከ ሁለት ዋት የሚደርስ ምድጃ የሰራ ሲሆን እነዚህን የፈጠራ ስራዎች ሲሰራም ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪነበር፡፡
የሳይንስናቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንዳስታወቀዉ ወጣቱ በአሁን ወቅት ከትምህርት ሰዓት ወጪ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባመቻቸለት እና እሱም በኦሮምኛ “ኮኬት” ብሎ በሰየማትአንድ ክፍል ውስጥ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *