በቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ማንነቷ ያልታወቀች ሴት ባደረሰችው ፍንዳታ 9 ሰዎች ተጎድተዋል
በቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ማንነቷ ያልታወቀች ሴት ባደረሰችው ፍንዳታ 9 ሰዎች ተጎድተዋል
አርትስ 20/02/2011
የቱኒዚያ የሃገር ውሰጥ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ድርጊቱ የአሸባሪ ቢመስልም ሴትየዋ ግን የመከላከያም ሆነ የአሸባሪነት ታሪክም ሆነ ንክኪ የላትም ፡፡
ፍንዳታውን በተመለከተ ክትትል እየተደረገ ቢሆንም፤እስካሁን በአደጋው የሞተ ሰው እንደሌለ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
እስካሁን ድረስ ድርጊቱን ፈፅሚያለው ብሎ ሃላፊነት የወሰደ አሸባሪ ድርጅትም ይሁን ሌላ ተቋም የለም፡፡
ቢቢሲ ከቦታው በሪፖርተሩ አረጋገጥኩት እንዳለው ፍንዳታው ኢላማ ያደረገው በአካባቢው የሚገኘውን የፖሊስ መቆጣጠሪያ ስፍራ ሳይሆን እንዳለቀረ ተናግሯል፡፡
በቱኒዚያ ከሶስት ዓመታት በፊት በተለያየ ጊዜ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች ደርሰው 60 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ መቀዛቀዙ ይነገራል፤የጎብኚዎች ቁጥርም አሽቆልቁሏል፡፡