ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዩሌን ሎፔቴጉይ አሰናበተ
ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዩሌን ሎፔቴጉይ አሰናበተ
አርትስ ስፖርት 20/02/2011
ስፔናዊው የ52 አመት አሰልጣኝ ዩሌን ሎፔቴጉይ፤ ዚነዲን ዚዳን ከማድሪድ አሰልጣኝነት ራሱን ካነሳ በኋላ የስፔን ብሄራዊ ቡድንን ተሰናብተው ነበር በአለም ዋንጫው ዋዜማ ሰኔ ወር ላይ ክለቡን የተረከቡት፡፡
ሶስት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን በተከታታይ ማሸነፍ የቻለው ማድሪድ ከ2001- 02 ወዲህ በላሊጋው አስቀያሚ አጀማመር ላይ ይገኛል፡፡
በሎፔቴጉይ የቤርናባው የአራት ወራት ከግማሽ ቆይታም ክለቡ ማግኘት ካለበት 30 ነጥቦች ውስጥ 14ቱን ብቻ ማሳካት የቻሉ ሲሆን ይባስ ብሎ በላሊጋው የኢል ክላሲኮ ደርቢ ጨዋታ በተቀናቃኛቸው ባርሴሎና 5 ለ 1 በኑካምፕ መረታታቸውን ተከትሎ ለስንብታቸው እውን መሆን ምክንያት ሁኗል፡፡
ሎስ ብላንኮስ በቀጣይ በእርሳቸው ምትክ አሰልጣኝ ለመሾም እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ጣሊያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ ቅድሚያ ግምት አግኝተዋል፡፡ አሁን ቡድኑን በጊዜያዊነት የተረከቡት የቀድሞው የክለቡ አማካይ ተጫዋች አርጀንቲናዊው ሶላሪ ሲሆኑ የወጣቶች ቡድን (የካስቲያው) አሰልጣኝ በመሆን በክለቡ እያገለገሉ ይገኛል፡፡
በቀጣይ ዕሮብ ማድሪድ በስፔን ንጉስ ዋንጫ ከሜሊያ ጋር ጨዋታውን ሲያከናውን ቡድኑን ይመሩታል፡፡