በአፍሪካ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የፍትህ ስርዓቱን ማጠናከር ይገባል ተባለ
በአፍሪካ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የፍትህ ስርዓቱን ማጠናከር ይገባል ተባለ
አርትስ 20/02/18
ይህ የተባለው የአፍሪካ ህብረትና የአሜሪካ መንግስት በጥምረት ባዘጋጁት ”ጥቃት ተኮር ጽንፈኝነትን የመከላከል ሳምንት” የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
ትላንት በአዲስ አበባ በይፋ የተጀመረው ለተከታታይ ሰባት ቀናት በሚቆየው ጥቃት ተኮር ጽንፈኝነትን የመከላከል ሳምንት ከሽብርተኝነትና ጽንፍ ከረገጡ አስተሳሰቦች የሚመነጩ ሌሎች ጥቃቶችን መዋጋትበሚቻልበት መንገድ ላይ ውያያት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡
መተባበር በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩነቶች የሚከበረውን ይህንኑ መድረክ በተመለከተ በአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ክፍል ተወካይ ወይዘሮ ኢናስ ሙሃመድ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅትበመካከለኛውና በምዕራብ አፍሪካ አገሮች ቦኮሃራም፤ በሰሜንና በምስራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ደግሞ አይኤስ እና አልሸባብ ስጋት ናቸው ብለዋል።
በሌላ በኩል በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ብሄርና ጎሳ ተኮር የሆኑ ጥቃቶች እንደዚሁም ፖለቲካን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በርካታ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ነው ብለዋል።
ሽብርተኝነት እንዲቀንስ፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም የዴሞክራሲ ባህል እንዲዳብር የአፍሪካ ህብረት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በአሜሪካ የፀረ-ሽብር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሚስ አሊና ሮማኖቪስኪ በበኩላቸው በአፍሪካ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ጠንካራ አቅምና የፍትህ ሥርዓት ያላቸው መንግስታት እንዲፈጠሩ አሜሪካ የማያቋርጥድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብተዋል።