ፈረንሳይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመታደግ የቀረበላትን የድጋፍ ጥሪ ተቀበለች
ፈረንሳይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመታደግ የቀረበላትን የድጋፍ ጥሪ ተቀበለች
አርትስ 20/02/2018
ፈረንሳይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመታደግ የቀረበላትን ጥሪ እንደተቀበለች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ገለፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ይህን ያሉት ከፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
ሰላምና ደህንነት፣ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ትምህርትና ባህል በጋራ ለመስራት ከተስማሙባቸው ዘርፎች መካከል ሲሆኑ ሀገራቱ የቆየ ወደጅነታቸውን በማጠናከር ለተሻለ ለውጥ እንደሚሰሩምተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አማካኝነት በኢትዮጵያ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለመደገፍ ሀገራቸው ዠግጁ እንደሆነች ገልፀዋል፡፡
ኢማኑኤል ማክሮን ከቀጠናው ሰላም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እያደረጉ ያሉትን ተግባር እንደግፋለን ብለዋል።
በተለይም በዶክተር አብይ ተነሳሽነት በኢትዮጵያና በኤርትራ የተፈጠረውን ሰላም በተመለከተ ልዩ አክብሮት እንዳላቸው ገልጸው ቀሪው የሰላም ሂደት የተሳካ እንዲሆንም ከጎናችሁ እንቆማለን ሲሉድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ከሁለት ወራት በኋላ የተጀመረውን ግንኙነት ለማጠናከር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም ተናግረዋል፡፡