በአዲስ አበባ ወንዞችና በዙሪያቸው 33 የተለዩ ቦታዎች መልሰዉ እንዲያገግሙ የሚያስችል ስራ ተጀመረ
አርትስ 13/02/2011
በአዲስ አበባ ወንዞችና በዙሪያቸው 33 የተለያዩ ቦታዎች መልሰዉ እንዲያገግሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች መጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞችና የወንዞች ዙሪያ ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት እንዳስታወቀው የከተማ ወንዞችና ምንጮች ተፋጥሯዊ ይዘታቸዉን ጠብቀዉ በሚፈሱበት ወቅት ለህብረተሰቡ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ይሰጡየነበረ ቢሆንም ከግዜ በኃላ በደረሰባቸዉ ሰዉ ሰራሽ ብክለት ለህብረተሰቡ የጤና እክል እየሆኑ ነው ብሏል፡፡
የጽ/ቤቱ አስተባባሪ አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ እንደተናገሩት በወንዞቹ ዙሪያ የሰፈሩ 150 ሺህ ዜጎች ደግሞ ችግሩን እንዲባባስ እንዳደረገው ገልፀው ከህብረተሰቡ የሚለቀቀው ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ እንዲሁም ኢንዳስትሪዎችናፋብሪካዎች በወንዞቹ ላይ የሚለቁት የተበከለ ፍሳሽ የወንዞቹ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ እነዚህን ችግሮች ከመሰረታቸዉ እልባት ለመስጠት ያስችለኛል ያለውን ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት በመጀመሪያዉ ዙር ብቻ በአዲስ አበባ ወንዞችንና የወንዞችን ዙሪያ 33 አካባቢዎች ተለይተው መልሰዉ እንዲያገግሙ እየተደረገ ሲሆን ከእነዚህ ወንዞች ውስጥ በሸራተን መልሶ ማልማት ዙሪያ፣ በቀጨኔወንዝ ላይ 6ኪሎ፣አፍንጮ በር፣ራስ መኮንን ድልድይ፣ሰራተኛ ሰፈር፣እሪ በከንቱን ይዞ የሚገኘዉን 15 ሄክታር መሬት በፓርክ ደረጃ ለማልማት ጥረት ላይ መሆኑን ጽ/ቤቱ አመልክቷል፡፡